Book Information

ያልታደለች ሃገር ህዝብ እና ሰራዊት

ብርጋዴር ጄነራል ዋሲሁን ንጋቱ

Description

     

    የመጽሐፉ መታሰቢያነት

    በኢህአዴግ መራሹ የኢፌዴሪ መንግሥት ምንም ወንጀልና ጥፋት ሳይገኝብኝ፣ ያለአንዳች ክስና ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝና ውሳኔ 10 ዓመት በግፍ ስታሰር፣ ከባድ ችግርና መንገላታት ለደረሰባት ለውድ ባለቤቴ ወ/ሮ መዓዛ መሸሻ እና ለልጆቼ መታሰቢያ እንዲሆንልኝና እንዲሁም ኢትዮጵያ አገራችን ዳር ድንበረዋ ተከብሮና አንድነቷና ሕልውናዋ ተጠብቆ፣ታፍራና ተከብራ በሰላም እንድትኖር ሲሉ፣ ከፍተኛ ተጋድሎ በማድረግ፣ መስዋዕትነት በመክፈል መተኪያ የሌላትን ክቡር ሕይወታቸውን በየጦር ግንባሩ ለሰዉ፣ ደማቸውን ላፈሰሱና አጥንታቸውን ለከሰከሱ ለ5 ዓመት ጀግኖች አርበኞች፣ ለኢትዮጵያ የመከላከያ ሚኒስቴር የቀድሞው የምድር ጦር፣ የአየር ኃይል፣ የባሕር ኃይል፣ የፖሊስ ሠራዊት አባላትና ላልተዘመረላቸው የሀገር ታላቅ ባለውለታ ለነበሩት ለሕዝባዊ ሠራዊት (ሚሊሺያ) ጀግኖች ፤ እንዲሁም ፣ አገራዊ ጥሪያቸውን ተቀብለው ግዳጃቸውን በአኩሪ ገድል ለፈጸሙት ፣ ለብሔራዊ ውትድርና አገልግሎት ዘማቾች እና የጦር ሜዳ የሙያ አጋሮቼ ለነበሩት ታንከኞች በሙሉ መታሰቢያ ይሁንልኝ።